ሰኞ ግንቦት 29 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ2014 አፈጻጸም በአዋሽ በመገምገም ላይ ነው።
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በመሩት በዚህ መድረክ ላይም የእያንዳንዱ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ያለፉት 10 ወራት አፈጻጸም ቀርቧል።
የአፈጻጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት የፕላን እና ልማት ሚንስትሯ ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፣ በዓመቱ ሀገሪቱ በውጫዊ እና ውስጣዊ ጫናዎች ውስጥ ብታልፍም፣ ኢኮኖሚውን እንቅስቃሴው ሳይስተጓጎል ማስቀጠል መቻሉን ተናግረዋል።
ለዚህም የበጋ ስንዴ፣ የሸቀጦች ወጭ ንግድ፣ ገቢ ምርትን በአገር ውስጥ መተካት እንዲሁም የህዳሴ ግድብ ሀይል ማመንጨትን ጨምሮ በዓመቱ የተከናወኑ ሥራዎች ትልቅ ፋይዳ እንደነበራቸው ተናግረዋል።







