ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከልና ለማስወገድ የተቀረፀውን ፍኖተ ካርታ የማስተዋወቅ ሥራ ተጀመረ

0
570

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሴቶች፣ ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስቴር በምሥራቅ አማራ ክልል ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ጎልቶ ከሚታይባቸው አምስት ዞኖች እና 30 ወረዳዎች ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት ድርጊቱን ለመከላከልና ለማስወገድ እንዲያስችል የተቀረፀውን ፍኖተ ካርታ ለማስተዋወቅ ያለመ መድረክ በደሴ ከተማ አካሂዷል።

መድረኩን አስመልክተው መልዕክት ያስተላለፉት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሚኒስትር አማካሪ አቶ መብራቱ ይመር እንደተናገሩት፣ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ መንግሥት በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈፀመውን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በተለይም ደግሞ ያለ እድሜ ጋብቻና የሴት ልጅ ግርዛት የሚያስከትለውን ዘርፈ ብዙ ጉዳት ከግምት ውስጥ በማስገባት እ.አ.አ 2025 ድርጊቱን ሙሉ በሙሉ ለማስቆም በለንደን በተካሐየደው ዓለም አቀፍ መድረክ ቃል ኪዳን መግባቱን አስታውሰው ለተፈፃሚነቱም በርካታ እርምጃዎችን እየወሰደ እንደሚገኝም አስረድተዋል።

በተመሳሳይ በአገር አቀፍ ደረጃ ያለው የኤች.አይ.ቪ ስርጭት፣ በዜጎች በተለይም በሴቶች ላይ እያደረሰ ስላለው ጉዳት፣ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊትና ኤች.አይ.ቪ ስላላቸው ቁርኝት እንዲሁም ድርጊቱን መከላከልና ማስቆም የቫይረሱን ስርጭት በመግታት ረገድ ስለሚኖረው ጠቀሜታ በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት ያሬድ አማካኝነት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጥቷል።

ቅጽ 1 ቁጥር 47 መስከረም 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here