የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና የሠራተኞቹ ጉዳይ በስምምነት ተፈታ

0
560

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በሠራተኞቹ መካከል በጥቅማ ጥቅም እና በሥራ ዕድገት መስፈርቶች ዙሪያ ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በውይይት መፈታቱ ተገለጸ።
ከ28 ሺሕ በላይ ሠራተኞች ያሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች ማኅበር፣ በባንኩ ግልጽ ሆነ የሥራ ዕድገት መስፈርት አለመኖር እንዲሁም ደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ማንሳታቸውን ተከትሎ፤ ጉዳዩን የፌዴራል ሠራተኛ እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሠሪ እና ሠራተኛ ጉዳይ ወሳኝ ቦርድ ሲመለከተው ቆይቷል።

በሠራተኛ ማኅበሩ እና በባንኩ አመራሮች መካከል በተደረጉ ውይይቶችም ለሥራ ዕድገት እንዲሁም በደሞዝ እና የጥቅማ ጥቅም ጉዳዮችን በተመለከተ ከስምምነት በመደረሱ ጉዳዩ መቋጨቱ ተገልጿል።

ለሥራ ላይ ዕድገት አምስት ግልፅ መስፈርቶች መዘጋጀታቸው የተገለጸ ሲሆን ባንኩ የደሞዝ እና የጥቅማ ጥቀም ጥያቄዎችን ለመፍታት በአዲሱ የበጀት ዓመት እስከ መቶ በመቶ ደሞዝ ጭማሪ ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ቅጽ 1 ቁጥር 47 መስከረም 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here