በደቡብ አፍሪካ አምስት ኢትዮጵያውያን በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር በቁጥጥር ሥር ዋሉ

0
439

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ አምስት ኢትዮጵያውያንን በሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። በቁጥጥር ሥር የዋሉት ኢትዮጵያውያን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ እና በዐሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያንን በሕገ ወጥ መንገድ አፍነው ሲያዘዋውሩ እጅ ከፍንጅ በመያዛቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

ሕገ ወጥ አዘዋዋሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሊውሉ የቻሉት ሦስቱን ወጣቶች አፍነው ለመልቀቅ ወደ ወላጆች በመደወል ለአንድ ልጅ 50 ሺሕ የደቡብ አፍሪካ ራንድ እንዲከፍሉ በማስገደዳቸው ነው። ወላጆችም አስቀድመው የልጆቻቸውን መሰወር ለፖሊስ አስታውቀው የነበረ ሲሆን ፖሊስ ባደረገው ያላሰለሰ ጥረት ሊያዙ ችለዋል።

ሦስቱ ወጣቶች ከዕገታው በፖሊስ ዕርዳታ እንዲለቀቁ የተደረገ እና ወደ ጊዜያዊ መጠለያ የተወሰዱ ሲሆን የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎችን በማካሔድ ላይ እንደሚገኝም ታውቋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 47 መስከረም 17 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here