ፍርድ ቤቱ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ በ10 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ አዘዘ

0
1151

ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እና ጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስትና በማስያዝ ከእስር እንዲለቀቁ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

ፍርድ ቤቱ፤ ፖሊስ በጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ እና በመስከረም አበራ ላይ እያደረገው ለሚገኘው ምርመራ ተጨማሪ ስድስት ቀናት መፍቀዱንም ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ትዕዛዙን ያስተላለፈው ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 30 ቀን 2014 ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here