አዲስ የሳተላይት ቴሌቪዥኖች ማሰራጫ በኢትዮጵያ ጀመረ

0
489

‹‹ኢትዮ ሳት›› የተሰኘ እና በርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን አካቶ የያዘ የሳተላይት ጣቢያ በኢትዮጵያ ጀመረ። ከኢትዮጵያ ብሮድካስተርስ ማኅበር፣ ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ባለስልጣን፣ ከዓለም አቀፍ የሳተላይት ኦፐሬተሮች  ከኤስ ኢ ኤስ ጋር  በመተባበር የተመሰረተው ጣቢያው በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ታዋቂ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን አቅፎ እንደሚይዝ ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ከመካከለኛው ምስራቅ እና ሰሜን አፍሪካ አገራት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ጋር በመደባለቅ ይተላለፉ እንደነበር ሳተላይት ጣቢያው መክፈቻ ወቅት ተነግሯል። የአሁኑ ሳተላይ ግን ኢትዮጵያዊያን ቴሌቪዥን ጣቢያዊች ራሳቸውን ችለው ያለምንም መቀላቀል በላቀ ጥራት ለተጠቃሚዎች እንዲደርሱ ምክንያት ይሆናል ተብሏል።

ሳተላይት ጣቢያው በ57 ዲግሪ ምስራቅ፤ ከ30 በላይ የኢትዮጵያ ተመልካች ያላቸውን ጣቢያዎች የሚያስተላልፍ ሲሆን ከ30ዎቹ ውስጥ አስራ ኹለት የሚሆኑት በላቀ ጥራት የሚገኙ እንደሆኑ ታውቋል። የሳተላይት ጣቢያው ከኢትዮጵያዊያን ጣቢያዎች ባለፈም በቀጣይ ተቀራራቢ ይዘት ያላቸውን ዓለም አቀፍ ጣቢያዎችን እንደሚያስተላልፍ ዕቅድ ተይዟል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here