ኢትዮጵያ የወጪ ንግድ የ69 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ጭማሪ አሳየ

0
937

ኹለት ወራትን ባስቆጠረው የ2012 በጀት ዓመት ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ዓለም አቀፍ አገራት ከተላኩት ምርቶች እና የወጪ ንግድ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ69 ነጥብ9 ሚሊዮን ዶላር ችማሪ ማሳየቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር አስታውቋል።

ሚንስቴሩ ጨምሮ እንደገለፀው፤ ከተያዘላቸው ዕቅድ በላይ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች ሙጫና ዕጣን፣ አበባ፣ የብርዕ አገዳ፣ኤሌክትሪክ፣ ጫት፣ የኬሚካልና የኮንስትራክሽን ግብዓት፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ጨርቃ ጨርቅ መሆናቸውን ይፋ አድርጓል።

የዕቅዳቸውን ከ75 በመቶ እስከ 99በመቶ ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች ደግሞ የጥራጥሬ ሰብሎች፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና ቡና ሲሆኑ፤ የዕቅዳቸውን  ከ50በመቶ እስከ 74በመቶ ክንውን ያስመዘገቡ ምርቶች የቅባት እህሎች፣ ታንታለም፣ የቁም እንስሳት፣ ስጋ፣ ባህር ዛፍ፣ ሰም እና ቆዳና የቆዳ ውጤቶች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል  ደግሞ ከተያዘላቸው ዕቅድ አንጻር የውጭ ምንዛሬ ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ያስመዘገቡ የወጪ ንግድ ምርቶች ወተትና የወተት ተዋጽኦ፣ ቅመማ ቅመም፣ ምግብ መጠጥና መድኃኒት ነክ፣ ወርቅ፣ ማር፣ ሌሎች ማዕድናት፣ የሥጋ ተረፈ ምርት፣ ሻይ ቅጠል፣ ብረታ ብረት እና ዓሣ መሆናቸውን የንግድና ኢንዱስተሪ ሚኒስቴር የወጪ ንግድ አፈጻጸም ሪፖርት ያሳያል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here