የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ ቀየረ

0
976

ለአለፉት በርካታ ዓመታት አዲስ አበባ ፖሊስ ሲጠቀምበት የነበረውን የደንብ ልብስ በአዲስ እና ዘመናዊ ልብስ መቀየሩ ተገለፀ። የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ምክትል ከንቲባ ዛሬ መስከረም 22/2012 አዲሱን የደንብ ልብስ በይፋ መርቀዋል።

በምረቃቱ ወቅት ምክትል ከንቲባው እንደተናገሩት፤ የከተማዋን ሰላምና ደኅንንት ለመጠበቅ እየሰራ ያለውን የፖሊስ ኃይል ለማዘመን ከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እየሰራ እንደሆነ አበክረው ገልፀዋል። ታከለ አያይዘውም ፤ በዘላቂነትም የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን የሚመጥን ዘመናዊ እና የተደራጀ የፖሊስ ሰራዊት ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ  ተናግረው የተመረቀው የአዲስ አበባ ፖሊስ የደንብ ልብስ የኮሚሽኑ አርማ ያለበት ሲሆን በሂደት ለኹሉም አባላት የሚሰራጭ ይሆናል፡፡

ከዚህ ቀደም የአዲስ አበባ ፖሊስ ከደንብ ልብስ ባሻገርም በቴክኖሎጂ የታገዘ የሊስ ኃይልን ለማደራጀት ኮሚሽኑ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱ የሚታወስ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here