የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ የሦስተኛ ዲግሪ መርሃ ግብር ሊጀምር ነው

0
710

የአማራ ክልል አመራር አካዳሚ በሦስት ተለያዩ ትምህርት ዘርፎች በዶክትሬት ዲግሪ ለማስተማር ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አማራ ክልል ኮሙኒኬሽን አስታውቋል። አመራር አካዳሚው በዶክትሬት ዲግሪ ሊጀምር ላሰበው መርሃ ግብርም ስርዓተ ትምህርቱን  በተመለከተ ምሁራንን አስገምግሟል።

አመራር አካዳሚው በዶክትሬት ደረጃ ለማስተማር ያቀዳቸው ትምህርት ዘርፎች በፖለቲካል ኢኮኖሚ፤በሰላምና ደህንነት እና በፐብሊክ ፖሊሲ እና ሊደርሺፕ እንደሆነ የአመራር አካዳሚው ዳይሬክተር ማተቤ ታፈረ (ዶ/ር) አስታውቀዋል። ማተቤ አያይዘውም ከዶክትሬት ዲግሪ በተጨማሪ በሕግና ኢኮኖሚክስ፤ በፕሮጀክት ማኔጅመንት እና በሰላምና እድገት የትምህርት ዘርፎች ደግሞ በማስተርስ ዲግሪ ደረጃ ለማስተማር ታልሞ ስርዓተ ትምህርቱ መዘጋጀቱን  ተናግረዋል።

አዲሱ ትምህርት መርሃ ግብር ይፋ በተደረገበት ወርክ ሾፕ ላይ በክብር እንግዳነት የተገኙት የአዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ  ዮሐንስ ቧያለው በበኩላቸው የአብዛኛዎቹ አፍሪካ አገራት ዋነኛ ችግር ብቃት ያለው አመራር እጦት ምክንያት መሆኑን በመጠቆም በእኛም አገር እርስ በእርስ የሚያባላን የአመራር ክህሎት እና ጥበብ በማጣታችን ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here