የኢትዮጵያ ቀዶ ሕክምና ማኅበር ኩባን ዓመታዊ ተሸላሚ አደረገ

0
598

ኢትዮጵያ ቀዶ ሕክምና ማኅበር ኩባ በሕክምናው ዘርፍ ለኢትዮጵያ ላበረከተችው አስተዋጽኦ እና ለባለሙያዎች በሰጠችው ስልጠና ዓመታዊ ሽልማት አበርክቷል።

በሽልማት ስነ ስርዓቱ ላይ የማኅበሩ ፕሬዘዳንት ደረጀ ጉልላት እንደተናገሩት ኩባ በዓለም አቀፍ ደረጃ በሕክምናው ዘርፍ የምታደርገውን ሰፊ እገዛ አድንቀው ኢትዮጵያን ጨምሮ ለበርካታ ዓለም አቀፍ አገራት የምትሰጠውን ነፃ የትምህርት ዕድልም በሰፊው አድንቀዋል። በነፃ የትምህር ዕድሉም 4ሽሕ የሚሆኑ ወጣት ኢትዮጵያዊያን ተጠቃሚ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ከእነዚህም ውስጥ በርካቶች በሕክምና ትምህርት ዘርፍ ያጠኑ ሲሆን ሃምሳ የሚሆኑት ደግሞ በሕክምና ስፔሻላይዝ ያደረጉ መሆናቸው ተገልጿል።

በ24ኛው አመታዊ የቀዶ ሕክምና ማኅበር ጉባኤ ላይ ከአርባ ዓመታት በላይ በመላው ኢትዮጵያ በሕክምናው ዘርፍ ድጋፍ እያደረጉ የኖሩ ኩባዊያን ዶክተሮችና የሕክምና ባለሙያዎች መኖራቸው በማኅበሩ ፕሬዘዳንት ተገልጿል። በታሪክም ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ የገቡት የውጭ አገር የቀዶ ሕክምና ሐኪሞች ኩባዊያን እንደሆነም በትውስታ ተነስቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here