ዳሰሳ ዘ ማለዳ ዓርብ መስከረም 23/2012

0
1170

1-በኢትዮጵያ ላለፉት 5 አመታት ለመንግስት ተቋማት የቢሮ ኪራይ ከ 2 ነጥብ6 ቢሊዮን ብር በላይ ማውጣቱን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ። በ2007 በጀት ዓመት ለቢሮዎች ኪራይ ይከፈል የነበረው ዓመታዊ ገንዘብ 257 ሚሊዮን ብር የነበረ ሲሆን በ2011 ደግሞ ወደ 888 ሚሊዮን ብር ማሻቀቡን ተገልጿል።ባለፉት ጥቂት ዓመታት 10 የፌደራል ተቋማት ቢሮ ተገንብቶላቸው ወደ ራሳቸው ቢሮ የገቡ ሲሆን ሌሎችም እየተገነባላቸው መሆኑን የገንዘብ ሚንስትር  ሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ሓጂ ኢብሳ ተናግረዋል።(ኢቢሲ)

………………………………………………………………………………

2–ኢትዮጵያ በፈረንጆች በ2021 የሚካሄደውን የዓለምአቀፍ የቴሌኮሙኒኬሽን ልማት ጉባዔን ለማስተናገድ ያላትን ምቹነት የሚገመግም ቡድን በአዲስ አበባ ግምገማውን አካዷዋል።ቡድኑ ጉባዔው ይካሄድበታል ተብሎ የሚታሰቡ የስብሰባ ማዕከላት ያላቸውን የስብሰባ አዳራሾች እና በተለይ የአገራት የቴሌኮሙኒኬሽን ሴክተር ሚኒስትሮች፣ የኅብረቱ የበላይ አካላት፣ ሰራተኞች እና የሥራ ኃላፊዎች ያርፉበታል ተብሎ የሚገመቱ ሆቴሎችን ተመልክቷል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………………………..

3-ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ እያደረገች ያለው አስተዋጽኦ የሚደነቅ መሆኑን የዓለም አቀፉ የሲቪል አቪዬሽን ካውንስል ፕሬዝዳንት  በርናንድ አሊዩ (ዶ/ር)  ከትራንስፖርት ሚንስትር  ዳግማዊት ሞገስ ጋር ባደረጉት ዉይይት ላይ ገልጸዋል።ፕሬዝዳንቱ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ እያደረገች ያለውን አስተዋጽኦ አድንቀው፣ ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እና ድጋፋቸው እንደማይለይም ተናግረዋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………..

4 የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር  ሙፈሪሃት ካሚል የጀርመን ፓርላማ አባል የሆኑትን ማርቲን ሹልዝ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።የጀርመን ፓርላማ አባሉ በአገሪቱ ላይ ያለውን ለውጥ አድንቀው ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በትብብር ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸዉ ተናግሯል።(አዲስ ማለዳ)

 

……………………………………………………………………………………….

5-የአዲስ አበባ ከተማ እየተከሰተ ያለው የአየር ብክለት መጨመር በነዋሪዎች ጤና ላይ የመተንፈሻ አካላት እና የልብ ሕመም ችግር እያስከተለ በመሆኑ፣ ይህን ችግር ለመከላከል የከተማ አስተዳደሩ የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ኮሚሽን ከUSEPA እና ከUNEP ጋር በመተባበር ለከተማዋ የአየር ጥራት ማኔጅመንት ዕቅድ የማዘጋጀት ፕሮጀክት ነድፎ በመተግበር ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

…………………………………………………………………………………….

6- የኢትዮጵያን ታላቁን ኅዳሴ ግድብ ለመሙላትና አገልግሎቱንም ለማስኬድ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የትብብር፣ ዘላቂነት ያለውና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያመጣ ስምምነት ላይ ለመድረስ በግብፅ፣ በኢትዮጵያና በሱዳን መካከል እየተካሄዱ ያሉትን ድርድሮች እንደምትደግፍ ዩናይትድ ስቴትስ  አስታወቀች።(ቪኦኤ)

………………………………………………………………………………………..

7-  ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራምፓሳ ልዩ መልእክተኛ የሆኑትን ጄፍ ራዴብ እና ኩሁሉ ባታን (ዶ/ር) ዛሬ መስከረም 23/2012  በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ልዩ መልዕክተኞቹ የፕሬዝዳንት ሲሪል ራምፖሳን የኹለቱን አገራት ታሪካዊ ግንኙነት ያነሳውን መልእክት ሲያስተላልፉ ግንኙነቱን ወደ ስትራቴጃዊ ደረጃ ከፍ ለማድረግም ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በደቡብ አፍሪካ ኦፊሴላዊ ጉብኝት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።(አዲስ ማለዳ)

 

 

………………………………………………………………………………………………

8 የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ ሒደት ከአንድ ወገን ብቻ እንዳይሆንና ግችትን የሚፈጥሩ እንዳይሆኑ አሳስቧል።(አብመድ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here