መነሻ ገጽዜናየእለት ዜናዳሸን ባንክ 230 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበትን ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል አስመረቀ

ዳሸን ባንክ 230 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበትን ዘመናዊ የመረጃ ማዕከል አስመረቀ

ሐሙስ ሰኔ 16 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ዳሸን ባንክ 230 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበትን፣ ዘመናዊና በግል የፋይናንስ ተቋም ደረጃ የመጀመሪያ የሆነውን “ቲር 3” (Tier |||) የተሰኘ የመረጃ ማዕከል በዛሬው ዕለት በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት አስመርቋል።

በዳታ ማዕከሉ ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይም የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴን ጨምሮ፣ የባንኮች ሥራ አስፈፃሚዎች፣ የተለያዩ ድርጅት ኃላፊዎች፣ የባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የባንኩ የበላይ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተውበታል።

ይህ በቻይናው የቴክኖሎጂ ኩባንያ ህዋዌ የተተከለው የመረጃ ማዕከል ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን ከ1 ሺህ ያላነሱ ሰርቨሮችና ሌሎች ተያያዥ የኔትወርክ መሳሪያዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው የተገለፀ ሲሆን፤ በጥገና ወቅትም መደበኛውን የባንኩን አገልግሎት ሳያቋርጥ ዓመቱን ሙሉ መስጠት የሚችል ነው ተብሏል፡፡

የመረጃ ማዕከሉ በአካባቢው የሚስተዋሉ የተለያዩ ክስተቶችን በመለየት ለማዕከሉ ዋና የመቆጣጠሪያ ክፍል መረጃ ማስተላለፍ የሚችል ሲሆን፣ ችግር ሲከሰትም ችግሩን በመለየት ስጋቶችን ለማስቀረት በሚችል ዓለማቀፋዊ ደረጃውን የጠበቀ ቴክኖሎጂን ያሟላ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ይህም የመረጃ ማዕከል ዘመናዊ የባንክ አገልግሎትን ከየትኛውም ቦታ ማግኘት የሚያስችልና ባንኩ የተለያዩ አዳዲስ አገልግሎቶችን ያለምንም ችግር ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያግዘው እንደሚሆን የባንኩ ፕሬዝዳንት አስፋው አለሙ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ባንኩ በዲጂታል ዘርፍ አዳዲስ አገልግሎቶችን በማስተዋወቅና የአገልግሎቱንም ደህንነትና ጥራት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ ኹነኛ ሚና እንደሚኖረውም ፕሬዝዳንቱ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

ይህ ማዕከል የዳሸን ባንክን ፍላጎት ከማሟላት ባሻገር በሥራ ላይ ለሚገኙ እና ወደ አገሪቱ የባንክ ኢንዱስትሪ ለሚቀላቀሉ የአገር ዉስጥም ሆነ የዉጭ ባንኮች እንዲሁም ለሌሎች ተቋማት አገልግሎት መስጠት የሚችል አቅም እንዳለውም ተነግሯል፡፡

ዳሽን ባንክ አገራችን ከወጪ ንግድ፣ ከዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንትና ድጋፍ እንዲሁም ዓለም ዓቀፍ ሀዋላ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ ለማሳደግም የበኩሉን ድርሻ በመወጣት ላይ የሚገኝ ባንክ መሆኑም በሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች