የኢትዮጵያን ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ያማከለ የቴሌቪዥን ሳተላይት አገልግሎት ተጀመረ

0
860

ለሀገራችን የመጀመሪያው የሆነ በኢትዮጵያ ያሉ ቴሌቪዥን ጣብያዎችን የሚያሰራጭ ሳተላይት አገልገሎት ላይ መዋሉ ተገለፀ። ኢትዮሳት ተብሎ የተሰየመው ሳተላይቱ በአሁኑ ሰዓት 30 ለኢትዮጵያ ተመልካቾች ብቻ የሚሰራጩ ቴሌቪዥን ጣቢያዎችን ይዞ የመጣ ሲሆን ኢትዮ ሳት ከሚያሰራጫቸው ጣቢዎች ውስጥ 12ቱ በከፍተኛ ጥራት (HD) ለህዝብ ፕግራሞቻቸውን የሚያደርሱ ይሆናል። በመሆኑም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ፕግራሞቻቸውን በከፍተኛ ጥራት (HD) እንዲያቀርቡ ያስችላል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ብሮድካስተሮች ዘርፍ ማህበር ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አማን ፍሰሃፅዮን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥኖች የሚያሰራጩበት ሳተላይት አቀማመጥ ለመካከለኛው ምስራቅና ለሰሜን አፍሪካ በዋነኝነት አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ጣቢያዎቹ የሚያቀርቧቸው ፕሮግራሞች የተቀላቀሉና ተመልካች ላይ ግራ የመጋባት ስሜትን የሚፈጥሩ ነበሩ” ብለዋል። “ተወዳጅ የሆኑትን የሀገር ውስጥ ጣቢዎች ወደአዲሱ የኤስ.ኢ .ኤስ ሳተላይት ማሸጋገራችን ለኢትዮጵያ ብቻ የተመደበ የሳተላይት አቅርቦት ከመፍጠራችን በተጨማሪ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጣቢያዎች በኤች ዲ (HD) እንዲቀርቡም ያስችላል” ሲሉም አክለዋል።

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ጣቢያዎችን በአንድ ቦታ አሰባስቦ ማሰራጨቱ የጣቢያዎቹን ተደራሽነት ከማሳደጉም በላይ በሀገር ወስጥ ለሚገኙ ተመልካቾች የሚመጥኑ ዓለም አቀፍ ጣቢያዎችን በማቅረብ የተመልካቾችን አማራጭ ያበዛል ተብሎ ይጠበቃል።

ተመልካቾች ኢትዮ ሳትን በየቤታቸው በቀጥታ ለመከታተል እንዲችሉ የሳታላይት ዲሻቸውን ወደ አዲሱ አቅጣጫ መቀየር የሚጠበቅባቸው ሲሆን አቅጣጫቸውንም የኤስ ኢ ኤስ ሳተላይት በሆነው ኤን ኤስ ኤስ-12 በ57 ድግሪ ምስራቅ ላይ በማድረግ ምርጫቸው የሆኑትን ጣቢያዎች መከታተል እንደሚችሉ ተገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 48 መስከረም 24 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here