መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለለት የንግድ ፓሊሲ ተዘጋጅቷል ተባለ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለለት የንግድ ፓሊሲ ተዘጋጅቷል ተባለ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነው የተባለው የንግድ ፓሊሲ ተዘጋጅቶ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር መግለጹ ተሰምቷል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ እንዳላማው መኮንን፣ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ነው የተባለው የንግድ ፓሊሲ ተዘጋጅቶ የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

በኢትዮጵያ ያለው የንግድ ሕግ ሦስት የተለያዩ ርዕዮት ዓለም ያላቸውን መንግሥታት ያገለገለ ነበር፤ ይሄንን በመገንዘብ ሕጉ ዘመኑን ታሳቢ አድርጎ ተሻሽሏል ነው የተባለው።

እንደ አገር በኢትዮጵያ የንግድ ፓሊሲ ኖሮን አያውቅም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ በአሁኑ ወቅት አገራዊ የንግድ ፓሊሲ ተዘጋጅቶ፤ ባለድርሻ አካላት ሁሉ ተሳትፈውበትና ዳብሮ ለመጽደቅ ከጫፍ መድረሱን ማብሰራቸው ተመላክቷል።

ይህ ፓሊሲ የአገሪቷን ንግድ ቁልፍ ችግሮች ለመፍታት እንዲችል ሆኖ ተዘጋጅቷል የተባለ ሲሆን፤ አሁን ያለውን የንግድ ምስቅልቅል የሚፈታ ነውም መባሉ ተዘግቧል።

ሌላው የንግድ ሚዛኑን ማስጠበቅ ትልቁ ሥራ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው የገለጹ ሲሆን፤ ባለፈው በጀት ዓመት የ18 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ ተደርጎ እንደ አገር ያገኘነው ገቢ 3 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ነው። ልዩነቱም 15 ቢሊዮን ዶላር ነው ብለዋል።

ይሄንን እውነት ለመቀየር በተወሰዱ ማሻሻያዎችና ጠንካራ ሥራዎች ዘንድሮ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 1 ቢሊዮን ዶላር ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

እንደ አገር ጠንካራ የኤክስፓርት ስትራቴጂ ተግባራዊ እየተደረገ ነው። በዚህም ከኖርንበት አካሄድ ተላቀን በአዳዲስ አካሄድ ምርትን ማብዛት፣ ዓይነቱን መጨመር እና የገበያ መዳረሻዎችን ማስፋት የሚል አካሄድን መከተል በመቻሉ ዘንድሮ ከአራት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘት ተችሏል ተብሏል።


ቅጽ 4 ቁጥር 193 ሀምሌ 9 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች