በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ይመለሳሉ ተባለ

0
1090

በተለያዩ የአፍሪካ እና መካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ከ12 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለሱ ሥራ በይፋ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም ለመገናኛ በብዙኀን ሳምንታዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ ከሳውዲ አረቢያ ውጪ በተለያዩ የአፍሪካና መካከለኛው ምሥራቅ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን ወደ አገራቸው የመመለሱ ሥራ ሰሞኑን እንደተጀመረ አሳውቀዋል።

ተመላሾቹ በታንዛኒያ፤ ማላዊ፤ ዛምቢያ፤ ዚምባቡዌ፤ ጁቡቲ፤ ሱዳን፤ የመን እና ኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ናቸው ተብሏል።
ከሳዉዲ አረቢያ ዜጎችን የመመለሱ እንቅስቃሴ ከታቀደው በበለጠ እየተከናወነ መሆኑን የተነገረ ሲሆን፤ መንግሥት በሳውዲ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ በእስር ቤቶችና በማቆያ ማእከላት የሚገኙ 102 ሺሕ ዜጎቹን ወደ አገር ቤት ለመመለስ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ከመጋቢት 21/2014 ጀምሮ ሲሠራ ቆይቷል ነው የተባለው። በአጠቃላይም 50 በመቶ ዜጎችን መመለስ መቻሉ ተመላክቷል።

ኹለተኛው ምዕራፍ ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 20/2014 እየተከናወነ መሆኑን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።


ቅጽ 4 ቁጥር 193 ሀምሌ 9 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here