ምንጭ፡-ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው (2022)
ሥራ አጥነት የብዙ አገራት ችግር ነው። ለአንዳንዶች የጥቂት ወራት አጀንዳ ሲሆን፣ ለአንዳንዶቹ ደግሞ ዘመናት የሚሻገር የቤት ሥራና ቀዳሚ አጀንዳ ይሆናል። እዚህም በዐስርቱ ዝርዝር የሚገኙ አገራት የሥራ አጥነት ጉዳይ የየእለት መብሰክሰኪያ ምክንያታቸው የሆኑ ናቸው።
የዓለም ባንክ በተለያየ ጊዜና ዘመን ያሰባሰበውንና በ2020 ይፋ ያደረገውን መረጃ ይዞ ዝርዝሩን ይፋ ያደረገው ወርልድ ፖፑሌሽን ሪቪው፤ ደቡብ አፍሪካ በከፍተኛ ሁኔታ ሥራ አጥነት ያለባት አገር ናት ብሏል። ታድያ ድህነት ውስጥ ለሚገኙ አገራት፤ ሥራ አጥነት ሲጨምር አብሮ የሚጨምረው የሕዝብ ብዛት እሴትና ሀብት ከመሆን ይልቅ የሚበረክተው ችግር እና ዝርፊያ መሆኑ አያጠራጥርም።
ቅጽ 4 ቁጥር 193 ሀምሌ 9 2014