ዳሰሳ ዘ ማለዳ ረቡዕ መስከረም 28/2012

0
718

1-የጥቅምት ወር የነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል የተወሰነ ሲሆን የአውሮፕላን ነዳጅ በመስከረም ወር ሲሸጥበት ከነበረው በሊትር ብር 25.56 በዓለም ወቅታዊ ዋጋ መሰረት ተሰልቶ በተገኘው ልዩነት 1 ብር ከ 07 ሳንቲም በመጨመር በሊትር ብር 26 ነጥብ 63 እንዲሸጥ መወሰኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታዉቋል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………….

2-ከፍተኛ የሆነ የሕዝብና የመንግስት ሃብት ወጪ ተደርጎባቸው በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ተገዝተው አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኙ የኤሌከርትሪክ መሰረተ-ልማቶች ኃላፊነት በጎደላቸው ግለሰቦች እየተሰረቁና አደጋ እየደረሰባቸው መሆኑን የኢትዮጵያ  የኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታዉቋል።ተቋሙ በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ማርጀት ምክንያት እየደረሰ ያለውን የኃይል መቆራረጥና መዋዥቅ ለመቀነስ እና የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማሳደግ ጥረት በማድረግ ላይ ባለበት ወቅት በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ እየደረሰ ያለው ስረቆት የተቋሙን ችግር ከባድ እንዳደረገበት አስታውቋል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………….

3- በዘንድሮው በጀት ዓመት በከተማ ደረጃ ለ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ወጣቶች ቋሚ የስራ እድል ለመፍጠር መታቀዱ የፌዴራል የከተሞች የስራ እድል ፈጠራ እና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዳይሬክተር አቶ ንዋይ አልታየ ገልጿል።በዓመቱ ይፈጠራል ተብሎ ከታሰበው ቋሚ እና ጊዜያዊ የስራ እድል ፈጠራ ውስጥ በኦሮሚያ 440  ሽሕ፣ በአማራ 314 ሽሕ፣ በደቡብ 286  ሽሕ፣  እንዲሁም በትግራይ 110  ሽሕ፣ ወጣቶች የስራ እድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………….

4-ፌስቡክ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገራት በዛምቢያ ፣ ሶማሊያ ፣ ቡሪኪና ፋሶ ፣ ኡጋንዳ ፣ ታንዛኒያ ፣ በዲሞክራሲያዊ ረፐብሊክ ኮንጎ ፣ ኮትዲቫር ፣ ጊኔ ኮናክሬ እና ጋና  ሐሰተኛ መረጃዎችን መቀነስ የሚያስችለውን ፕሮግራም መጀመሩን አስታዉቋል።ሶስተኛ ወገን መረጃ ማጥሪያ የተሰኘው ይህ ፕሮግራም ሐሰተኛ መረጃዎን ለመቀነስ እና ሐሰተኛ የፌስቡክ ገፆችን በመዝጋት ፣ እውነተኛ የዜና አማራጮችን ማስተዋወቅ እና የማያስፈልጉ መልዕክቶችን ለሚልኩ አካላት የገንዝብ ድጋፍ የሚያደርጉትን መከላከል ይሕ ፕሮግራም ከሚያከናውናቸው አሰራሮች ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………….

5-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖ እሁድ ጥቅምት 2/2012 በይፋ ያስመርቃል።  555 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት የሸጎሌ የአውቶቡስ ዴፖ 52 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው  ሲሆን ፤ በአንድ ጊዜ ከ250 እስከ 300 አውቶቡሶችን በተመቻቸ ሁኔታ የማቆም አቅም እንዳለው  የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ገልጿል።(ኢቢሲ)

……………………………………………….

6-በአዲስ አበባ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን በአዲስ በመተካቱ ሂደት ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የታክሲ አገልግሎት (ኤታስ) ከሚሰጡ 13 ተቋማት ጋር በተወያዩበት ወቅት የኤታስ አገልግሎት ሰጪ ተቋማቱ በከተማ አስተዳደሩ ረቆ በቅርቡ ይፋ የሆነው መመሪያ ቴክኖሎጂው ላይ ምንም ተፅዕኖ እንደሌለው በመግለፅ ሕጉን እንደማይቃወሙ እና ለተፈፃሚነቱ ከከተማ አስተዳደሩ ጎን በመቆም እንደሚሰሩ ገልፀዋል።(ዋልታ)

……………………………………………….

7-የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ላለፉት ኹለት ወራት ክትትልና ድጋፍ ከሚደረግባቸው የሰብል ወጪ ንግድ ምርቶች በመጠን 106ሽሕ 113 ነጥብ 40 ቶን እና በገቢ 136ነጥብ 84 ሚሊዮን  ዶላር ለማግኘት አቅዶ በአፈፃፀም በመጠን 101ሽሕ 476 ነጥብ 78 ወይም 95ነጥብ 63 በመቶ  እና በገቢ 139ነጥብ 63 ሚሊዮን  ዶላር  ወይም 102 በመቶ ።ካለፈዉ በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ክንውን ጋር ሲነፃፀር በመጠን 12ነጥብ 16 በመቶ  እና በገቢ ደግሞ 8ነጥብ 06  ሚሊዮን  ዶላር ጭማሪ ማሳየቱን ገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

 

……………………………………………….

8- በኳታር ዶሃ ለ17ኛ ጊዜ  ከመስከረም 16-25/2012 በተካሄደው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፕዮና ሲካፈል ቆይቶ በሁለት ወርቅ፣ አምስት ብር እና አንድ ነሐስ በድምሩ በስምንት ሜዳልያ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ 2ኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ዛሬ መስከረም 28/2012 አዲስ አበባ ሲገባ በርካታ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና የስፖርቱ ቤተሰቦች አቀባበል አድርገውለታል።(አብመድ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here