ኢትዮጵያ በ2003 በግብፅ የተከሰተውን የፖለቲካ ትኩሳት ተጠቅማበታለች ስትል ግብጽ አስታወቀች

0
488

ኢትዮጵያ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት በ2003 በግብጽ ተከስቶ የነበረውን የፖለቲካ ትኩሳት እና አለመረጋጋት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅማበታለች ሲሉ የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቦሊ ለግብጽ የሕዝብ እንደራሴ ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በሚመለከት አስቸኳይ ስብሰባ ከሕዝብ እንደራሴው ጋር ባደረጉበት ወቅት ኢትዮጵያ በግብጽ ተከስቶ የነበረውን አለመረጋጋት በመጠቀም የሕዳሴው ግድብን መገንባት እንደጀመረች እና ከግብጽ በተጨማሪ ሌሎች የተፋሰሱ አገራትንም እንዳላማከረች አስረድተዋል። ሙስጠፋ አያይዘውም ግብጽ ከአባይ ውሃ የመጠቀም ታሪካዊ መብቷን ለማስጠበቅ የግብጽ መንግሥት እና ሕዝብ በትጋት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል።

በአባይ ወንዝ ዙሪያ ባለፉት ዓመታት በርካታ ድርድሮችን ቢደረጉም ከኢትዮጵያ ወገን ግን ብዙ ተግዳሮቶች ገጥመውናል ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ሙስጠፋ ለምክር ቤታቸው አስታውቀው፤ በቅርቡ በተካሔደው ውይይት እንኳን አለመግባባቶች እንደነበሩ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here