ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን የሦስትዮሽ ውይይት አደረጉ

0
545

በቀጠናው ሰላምና ደኅንነት ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ደቡብ ሱዳን የሦስትዮሽ ውይይት አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ አዲሱ የሱዳኑ ጠቅላይ ሚንስትር አብደላ ሐምዶክ እና የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ሳልቫ ኪየር ማያርዴት ዛሬ ከሰዓቱን በሦስቱ ጎረቤት አገራት የሚታየውን ድንበር ተሻጋሪ የሰላም እና ደኅንነት ችግሮችን ርዕስ አድርገው እንደተወያዩ የሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርን ዋቢ አድርጎ ኒያልምቤዳ የዜና አውታር ዘግቧል።

ዛሬ መስከረም 29/2012 በቤተ መንግስት የተገነባውን አንድነት ፓርክ ምረቃ ለመታደም እና ለይፋዊ የስራ ጉብኝት የገቡት የኹለቱ አገራት መሪዎች ከሦስትዮሽ ውይይቱ ቀደም ብሎ ለየብቻ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር ውይይት አድርገው እንደነበር ታውቋል። በጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪ በርካታ ጎረቤት አገራት መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here