በጋምቤላ ከተማ የሰዓት እላፊ ገደብ ተጣለ

0
1051

አርብ ሐምሌ 8 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) በጋምቤላ ከተማ ካለው ወቅታዊ ሁኔታ ጋር በተያያዘ ሕገወጥ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር የሰዓት እላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኡገቱ አዲንግ እንደገለጹት፤ ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የሰዓት እላፊ ተጥሎ እንደነበር ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ለማህበረሰቡ ደህንነት ታስቦ የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ክፍተት መታየቱን አብራርተዋል።

በመሆኑም በከተማው የሰዎች እና የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን በመለየት ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ንጋቱ 11፡30 ድረስ የተጣለው ገደብ ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

በዚህም መሠረት ከአንቡላንስና ከፀጥታ ሀይል ተሽከርካሪ በስተቀር ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰዎች መንቀሳቀስ የሚችሉት ከንጋቱ 11፡30 እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት መሆኑን አስታውቀዋል።

በአሁኑ ወቅት በጋምቤላ ከተማ ሰላማዊ ሁኔታ መኖሩን ያመለከቱት ኃላፊው፤ በየደረጃው የሚገኙ የጸጥታ ሃይሎች የተጠናከረ ጥበቃ እያደረጉ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ኡገቱ አክለውም የፀጥታ ሀይሉ የከተማውን ደህንነት ለማስጠበቅ በሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ በየአካባቢው ተደራጅቶ መረጃ በመስጠት ጭምር እገዛ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here