በቀጣዩ ዓመት የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ካፒቴኖች ሙሉ በሙሉ ኢትዮጵያዊያንና ጅቡቲያዊያን ይሆናሉ

0
823

ከቀጣዩ ዓመት ጀምሮ ኢትዮ- ጅቡቲ የባቡር ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያዊያንና ጅቡቲያዊያን ካፒቴኖች እንደሚያዝ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካ አስታወቁ። ጥላሁን ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፤ ትራንስፖርት ስራው በይፋ ከተጀመረ 19 ወራትን ቢያስቆጥርም ባቡሩን በማንቀሳቀስ ረገድ ኢትዮጵያዊያን ሚናቸው አናሳ እንደነበርና እንዲያውም ሙሉ በሙሉ በቻይናዊያን ካፒቴኖች እንደሚንቀሳቀስ ተናግረዋል።

ይህንም ለመቅረፍ 65 ያህል ቁጥር ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የባቡር ካፒቴኖችን ወደ ቻይና በመላክ ለማሰልጠን እንደታቀደ ኢንጅነር ጥላሁን ለአዲስ ማለዳ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም ቻይናዊያን ፕሮፌሰሮችና ረጅም ልምድ ያላቸውን የባቡር ካፒቴኖች ወደ ኢትዮጵያ በማምጣት ስልጠና ይሰጥ የነበረ ቢሆን በቂ እንዳልሁነ መንግስት መገንዘቡንም ጥላሁን ገልፀዋል። አዲሱ እና በቻይና አገር የሚሰጣቸው ስልጠና ግን ሙሉ በሙሉ ስልጠናውን ቃጠናቀቁ በኋላ ለጥቂት ጊዜያትም እዛው ቻይና ውስጥ ባቡር እንደሚያሽከረክሩም ተገልጿል።

በቻይናው የኮንስትራክሽን ኩባንያ ሲሲኢሲሲ እና ሲአርኢሲየተገነባው ኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ጠንካራ ሥራ እየተሰራበት የሚገኝ ሲሆን ከካፒቴኖች በተጨማሪም በቀጣይ ደግሞ የጥገና ባለሙያዎችን እና ዋና መቆጣጠሪያ ጣቢያ የሚሰሩ ሰራተኞችንም ቀስ በቀስ በኢትዮጵያዊያን እንደሚተኩ አዲስ ማለዳ አረጋግጣለች።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here