የኢትዮጵያ አየር ኃይል ተዋጊ ጀት ተከሰከሰ

0
1042

ከአዲስ አበባ 103 ኪሎ ሜትር ርቀት በኦሮሚያ ክልል  ኤጄሬ  ከተማ ዛሬ መስከረም 30/2012  ከጠዋቱ 5 ሰዓት አካባቢ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር ኃይል የሆነ ተዋጊ ጄት ተከሰከሰ።

ጄቱ የጤፍ ማሳ ውስጥ የተከሰከሰ ሲሆን የአየር ኃይል እሳት አደጋ ብርጌድና የተለያዩ የፀጥታ አካላት በቦታው ተገኝተው እሳቱን ለማጥፋት ባድረጉት ርብርብ እሳቱን ለመቆጣጠር ተችሏል። አዲስ  ማለዳ ከአይን እማኞች ባገኘችው መረጃ እስከ ስድስት ሰዓት አካባቢ እሳቱ  ከኢጀሬ ምንጃር በሚወስደው ዋናው መንገድ ይታይ እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ ቀደም በኤጄሬ ከተማ አቅራቢያ በተከሰተ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት በሆነው የአውሮፕላን አደጋ የ157 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል። በተመሳሳይ ንብረትነቱ የአየር ኃይል የሆነ ሔሊኮፕተር በዚህ አካባቢ መከስከሱም  ይታወሳል።

ዛሬ አደጋ የደረሰበት ተዋጊ ጀትም  የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ይገኛል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here