ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ ከዓለም አቀፍ ተጽእኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ሆነው ተመረጡ

0
1071

የኢፌዲሪ ኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጽእኖ ፈጣሪ ከተባሉ አንድ መቶ ግለሰቦች መካከል አንዱ ሆነው ተመረጡ። ኢንጅነሩ በመንግስት የዲጂታል አሰራር ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪ በሚል እንደተመረጡ ታውቋል።

ተጽእኖ ፈጣሪ ተብለው ለመመረጥ አምስት መቶ ሰዎች የተወዳደሩ ሲሆን አንድ መቶ ተወዳዳሪዎች ተመርጠዋል ከዚህም ውስጥ ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ በመንግስት ኃላፊዎች ዘርፍ እንደተመረጡ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስቴር አስታውቋል። በቅርቡ በአገር አቀፍ ደረጃ የተካሔደውን የችግኝ ተከላ በቴክኖሎጂ ተደግፎ እንዲቆጠር በማድረግና ኢትዮጵያ በዐስር ዓመታት ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ እንደትሰለፍ በቴክኖሎጂ ዘርፍ እያደረጉ የሚገኘው እንቅስቃሴ ለመመረጣቸው አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በዚህ ውድድር በመንግስት ኃላፊዎች ዘርፍ ኢንጅነር ጌታሁን መኩሪያ፣ የሎስ አንጀለስ ከንቲባ ኤሪክ ጋርሲቲ፤ የካናዳ የዲጂታል ገቨርንመንት ሚኒስትር ጆይሲ ሙራይ ቀዳሚውን ስፍራ እንደያዙ ተገልጿል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here