ዳሰሳ ዘ ማለዳ ዓርብ መስከረም 30/2012

0
1019

1-በተያዘው በጀት ዓመት የከተማ አስተዳደሩ በመሃል ከተማ የ500 ሺ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ በተለያዩ አማራጮች ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታዉቋል።የቢሮው ኃላፊ ኢንጂነር ሰናይት ዳምጠው የከተማ አስተዳደሩ በ2012 ቀደም ሲል ከነበሩ ዲዛይኖች ላይ መጠነኛ ማሻሻያ በማድረግ 500ሽሕ መኖሪያ ቤቶችን በከተማው ለማስገንባት በተለያዩ የግንባታ አማራጮችን ይዞ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፀዋል።በተጨማሪም በግንባታ ላይ የሚገኙ 139 ሽሕ በላይ ቤቶች ግንባታቸውን በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች እንደሚተላለፉ ተገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………..

2-የራሳቸው ቄራ ሳይኖራቸው የኤክስፖርት ቄራዎችን ተከራይተው የእርድ አገልግሎት በማግኘት ሥጋ ወደ ውጪ የሚልኩ ነጋዴዎች መታገዳቸውን ንግድና ኢንዱስት ሚኒስቴር አስታወቀ ።እገዳው ከጥቅምት 5/2012 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ተገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………..

3 በመጪው እሁድ በአዲስ አበባ በሚደረገው ሰልፍ ላይ ልትሳተፉ ነው በሚል ከአማራ ክልል በደጀን እና ጎሓ ፂዮን መስመር ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩ መንገደኞች ወደ መጡበት ወደ አማራ ክልል እንዲመለሱ ተደርገዋል። ከመንገደኞች ውስጥም ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች እና የሐኪም ቀጠሮ የነበራቸው ግለሰቦች እንደነበሩ የአይን እማኞች ተናግረዋል። (አብመድ)

………………………………………………………..

4-የአዲስ አበባ ከተማ የትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል ህንጻ ግንባታ እሁድ ጥቅምት 2/2012 ሊጀመር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አስታዉቋል።ህንጻው ከመሬት ስር የሚገነቡ አራት ወለሎች የሚኖሩት ሲሆን፤ ከትራፊክ መቆጣጠሪያ ማዕከል በተጨማሪ መረጃ ማደራጃ ክፍሎች፣ የወንጀልና የአደጋ መከላከያ መረጃ ቢሮዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን ያካትታል።(ዋልታ)

………………………………………………………..

5-የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በ2011 በጀት አመት በአክሲዮን እና የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬቱ አማካኝነት ለተለያዩ የአክስዮን እና የንግድና ዘርፍ ማህበራት ባደረገው ድጋፍ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን አስታዉቋል።በተጠናቀቀው በጀት አመት ከተለያዩ አክሲዮን ማኅበራት 45 ቅሬታዎች መነሳታቸውን ጠቁመው የ42ቱ ጥያቄ መልስ ማግኘቱን እና በ3ቱ ላይ የረጅም ሂደትን የሚጠይቅ በመሆኑ ጉዳያቸው እየታየ መሆኑን የአክስዮንና የንግድና ዘርፍ ማህበራት ጉዳዮች ዳይክቶሬት ዳይሬክተር አብይ መሃመድ ገልጸዋል።(አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………..

6- የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በ2011 በመዲናዋ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ የ10ኛ እና 12 ክፍል የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የገንዘብ ስጦታ አበረከተ።በ2011 በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ከፍተኛ ውጤት ላመጡ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እንደየ ደረጃቸው ከ5 ሽሕ እስከ 10 ሽሕ ብር ስጦታ ተብርክቶላቸዋል።በተመሳሳይ መልኩ ለ10ኛ ከፍል ተማሪዎችም ከ3 ሽሕ እስከ 5 ሽሕ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ)

………………………………………………………..

7-የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን ለ3 ሺህ 348 ሄክታር መሬት የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር መቀበሉን አስታዉቋል። ኮርፖሬሽኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በፓርኮቹ ልማት፣ ኦፕሬሽን ጥናት፣ የግንባታ እና የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም የመሬት ግዥና ርክክብ ላይ ውይይት አድርጓል። በኮርፖሬሽኑ ስር ከሚገኙ 12 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ሰባቱ ሥራ ላይ ሲሆኑ እነዚህም ለ50 ሺህ ቀጥተኛና ለ55 ሺህ ዜጎች ተዘዋዋሪ የሥራ ዕድል መፍጠር እንደቻሉ የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለሊሴ ነሜ ገልጸዋል።(አመብድ)

………………………………………………………..

8- ዛሬ መስከረም 30/2012 በሸራተን አዲስ የብሔራዊ የሎጅስቲክስ ስትራቴጂ ሰነድ ከ2011 እስከ 2020 ስድስት መሰረታዊ ስትራቴጂዎችን ያስቀመጠዉን የትራንስፖርት ሚንስቴር ሚንስትር ዳግማዊት በተገኙበት  ለባለድርሻ አካላት አስተዋውቋል።የሎጅስቲክስ ስርዓቱን በቀጣይ አስር አመታት ወስጥ ማሸጋገርን አላማ ያደረገ “በ2020 መጨረሻ የሎጅስቲክስ ስርዓታችን የአገራችን የንግድና የኢንቨስትመንት እድገት በማሳላጥ ከአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ማየት” በሚል ራዕይ በተዘጋጀ መድርክ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል ።(አዲስ ማለዳ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here