የኮሪያ ኤክስፖርት -ኢምፖርት ባንክ ለኢትዮጵያ 170 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አበደረ

0
496

በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ደካማ በሆነባቸዉ የአገራችን አካባቢዎች ለማስፋፊያ የሚዉል ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ 170 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ቀላል ብድር ከኮሪያ ኤክስፖርት -ኢምፖርት ባንክ ጋር የብድር ስምምነት ተፈረመ።

ፕሮጀክቱ በዋናነት አዳዲስ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መገንባት፣ አዳዲስ የመጀመርያ ደረጃ የሥርጭት መስመሮችን (substations) መገንባትና ማስፋፋት እና የፕሮጀክቱን ኢንጅነሪንግና ማኔጅመንት አቅም መገንባት እንዲሁም የቴክኒካል እገዛ ማድረግ እንደሚሠራ ተገልጿል።

ፕሮጀክቱ በሚካሔድባቸዉ አካባቢዎች ለሚካሔዱ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እንቅስቃሴዎች በቂና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንዲኖር በማስቻል በአገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት የበኩሉን አስተዋጽዖ የሚያበርክት ሲሆን በተጨማሪም ለፕሮጀክቱ ማስፈፀሚያ የሚዉለዉ ገንዘብ አነስተኛ ወለድ (እንደ አግባብነቱ ከወለድ ነፃ ሊሆን የሚችል) እና ወጪ የሚታሰብበት እንዲሁም ብድሩ የ15 ዓመት የችሮታ ጊዜን ጨምሮ በ40 ዓመታት ጊዜ ዉስጥ ተከፍሎ እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 49 ጥቅምት 1 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here