በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተቋረጠው የቪዛ አገልገሎት ተጀመረ

0
430

በሱዳን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦት የነበረውን የቪዛ አገልግሎት መጀመሩን ገለፀ። በካርቱም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መስከረም 25 ባወጣው ማስታወቂያ የቪዛ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ አቋርጦ የነበረ ሲሆን፣ ተቋርጦ የነበረውን የተጓዦች የቪዛ አገልግሎት ረቡዕ መስከረም 28 ቀን መጀመሩን አስታውቋል።

የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት፣ የቪዛ አገልግሎት ለመስጠት የሚለጠፉ ስቲከሮች በኤምባሲው በማለቃቸው ለኹለት ተከታተይ ቀናት ቪዛ አገልግሎት ለመስጠት ችግር አጋጥሞ እንደነበር የገለፁ ሲሆን፣ የአገልገሎቱ መቋረጥ በተወሰኑ ተገልጋዮች ላይ እንግልት እና ቅሬታ ፈጥሮ ነበር ብለዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከኢትዮጵያ ኢምግሬሽን እና ዜግነት ዋና መምሪያ ስቲከሮችን በመውሰድ ረቡዕ መስከረም 28 ቀን አገልግሎቱ እንዲጀመር ተደርጓል። ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን በርካታ ሰዎች እንደሚጓጓዙ የገለጹት ነቢያት፣ የስቲከሮች ማለቅ ከዛ ጋር የተያያዘ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።

ቅጽ 1 ቁጥር 49 ጥቅምት 1 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here