መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበዶሮ ላይ ተከስቶ የነበረው በሽታ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

በዶሮ ላይ ተከስቶ የነበረው በሽታ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተገለጸ

በዶሮ ላይ ተከስቶ የነበረው በሽታ በቁጥጥር ሥር በመዋሉ በዶሮ ውጤቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የግብይትና የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማኅበር ገለጸ።

ባለፉት ወራት በአንዳንድ የኢትዮጵያ ክፍሎችና በአንዳንድ የዶሮ እርባታዎች ላይ የዶሮ በሽታ ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማኅበር ጋር እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በሽታዉን የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ገልጿል።

በሽታዉን ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ በጊዜያዊነት በዶሮና የዶሮ ምርቶች ላይ ጊዜያዊ የግብይትና የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎ የቆየ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት በሽታዉ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማኅበር አስታውቋል።

በዚህም መሠረት የዶሮ ውጤቶች (እንቁላልና የዶሮ ስጋ) ላይ በግብርና ሚኒስቴር ተጥሎ የነበረው የግብይትና እንቅስቃሴ ገደብ በመነሳቱ፣ ማኅበረሰቡም ሆነ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቹን መገበያየት እና ያለምንም ስጋት መመገብ እንዲሁም መጠቀም የሚቻል መሆኑም ተገልጿል።


ቅጽ 4 ቁጥር 195 ሐምሌ 23 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads
- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች