መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበኦሮሚያ ክልል ከ178 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 3 ሺሕ 583 ባለሃብቶች...

በኦሮሚያ ክልል ከ178 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 3 ሺሕ 583 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱ ተገለጸ

የኦሮሚያ ክልል በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከ178 ቢሊዮን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ 3 ሺሕ 583 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፍቃድ መሰጠቱን ገለጸ፡፡

በዚህም ክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሻለ የኢንቨስትመንት ፍሰት አስተናግዷል ነው የተባለው።

የኢንቨስትመንት ፍቃድ የተሰጣቸው ባለሃብቶች ከተሰማሩባቸው መስኮች መካከል ማኑፋክቸሪንግ፣ የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ፣ ኮንስትራክሽን፣ ሆቴልና ቱሪዝም፣ ማእድንና ቡና ልማት እንደሚገኙበትም ተመላክቷል፡፡

በተመዘገበው የኢንቨስመንት ፍሰት ውስጥ ወደ ባለሃብትነት የተሻገሩ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮችና ኢንተርፕራይዞች ተሳትፎ ከፍተኛ እንደሆነም ተገልጿል።

ባለሀብቶቹ በተሰማሩባቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ለ534 ሺህ ዜጎች በቋሚና በጊዜያዊነት የሥራ እድል መፍጠር የሚችሉ መሆናቸውም ነው የተነገረው፡፡

በአዳማ ከተማ ብቻ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 130 የሚሆኑ ባለሃብቶች የኢንቨስመንት ፍቃድ መውሰዳቸው ተጠቁሟል፡፡

በበጀት ዓመቱ የኢንቨስትመንት ፍቃድ ከወሰዱ ውስጥ 91 የሚሆኑት ቀጥተኛ የኢንቨስመንት ፍቃድ የተሰጣቸው ባለሃብቶች ሲሆኑ፣ 39 የሚሆኑት ደግሞ ወደ ኢንቨስትመንት የተሸጋገሩ አርሶ አደሮችና ኢንተርፕራይዞች መሆናቸውን ነው የተብራራው።

ባለሃብቶቹ በሙሉ አቅማቸው ሥራ ሲጀምሩ ከ42 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድል የሚፈጥሩ መሆናቸውም ተመላክቷል፡፡


ቅጽ 4 ቁጥር 196 ሐምሌ 30 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች