የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች እንደሚኖሩት ተገለጸ

0
1298

እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች እንደሚኖሩት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት ገለጸ፡፡

ምክር ቤቱ የብዝኃ ዋና ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከክልሉ ስድስቱም ዞኖች ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል፡፡

በውይይት መድረኩ የብዝኃ ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ቦንጋ፣ ተርጫ፣ ሚዛን አማን እና ቴፒ እኩል ደረጃ ያላቸው የክልሉ ዋና ከተሞች ይሆናሉ እንደሚል ተጠቁሟል፡፡

ቦንጋ ከተማ የፖለቲካ እና የርዕሰ መስተዳድሩ መቀመጫ፣ ተርጫ የክልሉ ምክር ቤት መቀመጫ፣ ሚዛን አማን የዳኝነት አካል መቀመጫ እንዲሁም ቴፒ የብሔረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫ እንደሚሆኑም በረቂቅ አዋጁ ላይ ሰፍሯል፡፡

የክልሉ ዋና ከተሞች አራት እንዲሆኑ የተደረገው ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ መሆኑም ነው በረቂቅ አዋጁ ላይ የተጠቀሰው፡፡

ረቂቅ አዋጁ በቀጣይ በክልሉ ምክር ቤት ጸድቆ የሚተገበር ከሆነ፣ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል እኩል ደረጃ ያላቸው አራት ዋና ከተሞች ያሉት የመጀመሪያው ክልል እንደሚሆን ተመላክቷል፡፡


ቅጽ 4 ቁጥር 196 ሐምሌ 30 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here