ኖኪያ በኢትዮጵያ ከሦስት መንግስታዊ መስሪያቤቶች ጋር ስምምነት ሊፈራረም ነው

0
782

ግዙፉ የፊንላንድ የቴክኖሎጂ ኩባንያ እና በቴሌኮም ዘርፍም ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው ኖኪያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ከሦስት የመንግስት ኩባንያዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ሊፈራረም ነው። ኩባንያው ከሳይንስና ኢኖቬሽን ሚኒስቴር፣ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲሁም ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የመግባቢያ ሰነዱን እንደሚፈራረም ኩባንያው ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ የሚሰጠውን የትምህርት ጥራት፣ የምርምርና ፈጠራ ደረጃን ለማገዝ የሚያስችል ሲሆን ለተማሪዎችም ስልጠና የሚሰጥበት ዕድል እንደሚመቻችም አዲስ ማለዳ ከኖኪያ ኩባንያ ያገኘችው መረጃ ያመላክታል።

ጥቅምት 4/2012 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አምስት ኪሎ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የስብሰባ አዳራሽ የሚኒስቴር መስሪያቤቶች ሚንስትሮችና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍረህይወት ታምሩ የሚገኙ ሲሆን፤ የኖኪያ ኩባንያ የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተርም ኖኪያን ወክለው እንደሚፈራረሙ ታውቋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here