የእነ ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ የዋስትና መብታቸው ተፈቀደላቸው

0
725

 

የአማራ ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች የነበሩትና ከሰኔ 15ቱ ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጥረው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የነበሩት ብርጋዴር ጀነራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል መላኩ አለበል፣እና ኮሎሌል ባምላኩ የዋስትና መብታቸው ተፈቅዶላቸዋል። እያንዳንዳቸው በ10 ሽሕ ብር ዋስ እንዲለቀቁ የተፈቀደላቸው ሲሆን ጉዳያቸውንም በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ የአማራ ክልል ዐቃቤ ሕግ ማስታወቁን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ይፋ አድርጓል።

ከምርመራ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች የተጣሩ መሆናቸውንና ተጠርጣሪዎቹ  ኃላፊነታቸውን ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም የሚለው ጭብጥ ዋስትና የሚያስከለክል አለመሆኑን ዐቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ መግለጹን የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የክልል ዐቃቤ ሕግ ኢዮብ ጌታቸው ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

ጉዳዩን የተመለከተው ፍርድ ቤትም ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያቸውን በውጭ ሆነው እንዲከታተሉ እያንዳንዳቸው የ10 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲወጡ ያዘዘ ሲሆን

በዚህ መሠረትም ተጠርጣሪዎቹ ዋስትና አቅርበው ከሰዓት በኋላ መውጣታቸውን አቶ ኢዮብ ለአብመድ አረጋግጠዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here