ዳሰሳ ዘ ማለዳ ሰኞ ጥቅምት 3/2012

0
657

1-ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ በብሔራዊ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት 300 ሺሕ ተማሪዎችን የሚያካትተው የምገባ መርሐ ግብር በይፋ አስጀምረዋል።በምገባ መርሐግብሩ ላይ ከ10 ሺሕ በላይ እናቶች ምግቡን በማቅረብ ስራ ላይ ተሰማርተው የስራ እድል እንዲያገኙ ተደርጓል።ባለፈው አመት 70 ሺህ ተማሪዎች ሲያሳትፍ የቆየው የምገባ መርሀግብሩ በተያዘው አመት ቁጥሩ ወደ 300ሺሕ ተማሪዎች ከፍ ብሏል። (አዲስ መለዳ)

 

……………………………………………………………

2-ኢትዮጵያ ከሳውዲ ዐረቢያ ጋር ያላትን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር ያስፈልጋል ሲሉ በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የንግድ ማስፋፊያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተናገሩ።ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ የሳውዲ አረቢያ አምባሳደር ሳሚ ጃሚል አብዱላህ ጋር  ተወያይተዋል።ኃላፊዎቹ በውይይታቸው ኹለቱ አገራት ያላቸው የንግድና ኢኮኖሚ ግንኙነት ይበልጥ ሊጠናከር በሚችልባቸው ጉዳዮች እንዲሁም የንግድ ምክር ቤት ለማቋቋም እና የንግድ ጉባኤ ለማካሄድ በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል ።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………

3–ዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቀን “ለአደጋ የማይበገር አቅም እንገንባ” በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ለ10ኛ ጊዜ ጥቅምት 3/2012 በሒልተን ሆቴል ተከብሯል።የተለያዩ ጥናቶች ቀርበዉ ዉይይት የተካሄደባቸዉ ሲሆን የሰዉ ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎችን ለመቀነስ ትኩረት ተሰቶ እየተሰራ መሆኑን ተገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………

4-የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር  ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ጥቅምት3/2012 ደቡብ ሱዳን ጁባ ገብተዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጁባ ቆይታቸውም የሱዳን የሽግግር መንግስትን ከታጣቂ ተቃዋሚ ኃይሎች ጋር ለማስታረቅ በሚደረግ የኢጋድ አባል አገራት የመሪዎች የስብሰባ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንን በመምራት ይሳተፋሉ። (ፋና ብሮድካስቲንግ)

……………………………………………………………

5-በደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ጥቅምት 2/2012 ማታ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ኮሙኒኬሽን አስታወቋል።በአደጋው 5 መኖሪያ ቤቶች አሁንም በአፈር ተሸፍነው የሚገኙ ሲሆን የሰዎችን ሕይወት ለማዳን በኤክስካቫተር በመታገዝ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የኮንታ ልዩ ወረዳ የህዝብ ግንኙት ኃላፊ  ፋሲካ ሙሉጌታ ተናግሯል።(ኢቢሲ)

……………………………………………………………

6-ከጅግጅጋ ከተማ እስከ ሓርሞካሌ መገንጠያ 104 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ዛሬ ጥቅምት 3/2012 ተጀመረ።መንገዱ ከድሬዳዋ እስክ ደወሌ ከተሰራው የክፍያ መንገድ ጋር የሚያገናኝ ሲሆን ቀደምሲል ከጅግጅጋ ተነስቶ  በሐረር-ደንገጎ በኩል 202 ኪሎ ሜትር የነበረውን ጉዞ ወደ 99 ኪሎ ሜትር ይቀንሳል።ፕሮጅክቱ ከመንግስት በተመደበ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚሰራ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ ተናግሯል።(ዋልታ)

……………………………………………………………

7 በአፋር ክልል አፋምቦ ወረዳ ሜጉ ቀበሌ የታጠቁ ኃይሎች በፈፀሙት ጥቃት የ16 ሰዎች ህይወት አለፈ።ጥቃቱ የተፈፀመው ቅዳሜ ጥቅምት1/2012  ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ምሽት ድረስ መሆኑን የአፋር ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አህመድ ኡመድ ተናግረዋል።ጥቃቱ በተሸከርካሪ የታገዘ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የሰነድ ማስረጃዎችን ማግኘት እንደተቻለም ተችሏል።(ዋልታ)

……………………………………………………………

8-በጋምቤላ ከተማ ኮድ 3 AA 55966 የሆነ FSR መኪና 38 ክላሽኒኮቭ ሕገ ወጥ መሣሪያ  በግለሰብ ግቢ ተደብቆ ባለበት በመከላከያ ሰራዊት ፣በፌደራል ፖሊስ እና ጉምሩክ ሰራተኞች ባደረጉት የተጠናከረ ስራ መያዙን የገቢዎች ሚኒስትር አስታዉቋል።(አዲስ ማለዳ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here