በመጀመሪያው ሩብ አመት ከዕቅድ በላይ ገቢ ተሰበሰበ

0
832

ሐምሌ 1/2011 የጀመረው አዲሱ በጀት ዓመት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ብቻ ከታሰበው በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚንስቴር አስታወቀ። ሚንስቴሩ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 56 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ የተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቆ ነገር ግን 57 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጿል።

የዕቅዱን 102 በመቶ ማሳካት የቻለው ገቢዎች ሚንስቴር ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ12 ነጥብ 9 ቢሊዮን ብር ልዩነት ወይም 29 በመቶ ልዩነት መኖሩን ይፋ አድርጓል። በሩብ ዓመቱ ከተሰበሰበው ገቢ 54 በመቶ ያህሉ ከአገር ውስጥ ገቢ የተሰበሰበ ሲሆን የተቀረው 46 በመቶ ደግሞ ከጉምሩክ ቀረጥ የተሰበሰበ መሆኑን ከገቢዎች ሚንስቴር የተገኘው መረጃ ያመላክታል።

ይህ አፈፃፀም በየወሩ ሲተነተንም በሀምሌ ወር 18 ቢሊዮን ብር ፤በነሀሴ ወር 20.2 ቢሊዮን ብር እና በመስከረም ወር ደግሞ 19.1 ቢሊዮን ብር በአጠቃላይ በሩብ ዓመቱ 57.3 ቢሊዮን ብር ተሰብስቧል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here