መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናበፍራፍሬ እሴት ሰንሰለት ዙሪያ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን የዳሰሰ የፖሊሲ ውይይት ተካሄደ

በፍራፍሬ እሴት ሰንሰለት ዙሪያ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን የዳሰሰ የፖሊሲ ውይይት ተካሄደ

የእርሻ ውጤቶች እና የማቀነባበሪያ ዘርፉ በብዙ ችግሮች የተተበተበ እና ከሌሎች አገራት ጋር ሲወዳደር ገና ብዙ እንደሚቀረው የአዲስ ቻምበር ጥናት ማመልከቱ ተዘግቧል።

የፍራፍሬ ልማት በኢትጵያ የ10 ዓመት የኢንዱስትሪ የልማት መርሐግበር ውስጥ የቅድሚያ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፍ አንዱ ነው ተብሏል።

ነገር ግን፣ በመሬት ላይ ያለው እውነታ የተባለውን ያህል አይደለም ያለው ጥናቱ፤ አገራችንም ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን የውጪ ምንዛሬ እንዳላገኘች ተጠቁሟል ።

የአዲስ አበባ ንግድ ም/ቤትም ይህን የተመለከተ አንድ ጥናት በማስጠናት ከባለድርሻዎች ጋር የፖሊሲ ውይይት ያካሄደ ሲሆን፤ የዘርፉ ባለሙያ ታምራት ታደለ የቀረበው የጥናት ወረቀት ኢትዮጵያ ስድስት የሚሆኑ ዋና ዋና የፍራፍሬ ኮሪደሮች አላት ማለታቸው ተነግሯል።

እነዚህም የስምጥ ሸለቆ ሐይቆች፤ የአባያ፤ የጣና ተፋሰሶች፤ የቤንሻነጉል ጉሙዝ፤ የጅማ፤ የራያ እና የሐረርጌ ሸለቆዎች ናቸው። በአመት የሚሰበሰበው ምርት ደግሞ ወደ 1 ሚሊየን ቶን አቮካዶ፤ ብርትኳን፤ ሙዝ፤ ፓፓያ እና ስትሮቤሪ የመሳሰሉት ፍራፍሬዎች ናቸው ተብሏል።

እንደ ጥናቱ ከሆነ 90 በመቶ የሚሆነው የአገራችን የፍራፍሬ ምርት የምትገዛው ጎረቤት አገር ጂቡቲ ስትሆን፤ እስከ ባለፈው ኹለት አመት ድረስም ከዘርፉ የሚገኘው የውጪ ምንዛሬ ኹለት ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ያህል ብቻ ነው።


ቅጽ 4 ቁጥር 197 ነሐሴ 7 2014

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች