በዘንድሮው መኸር ከ2 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ በትራክተር ታርሷል ተባለ

0
1227

ግብርናውን ለማዘመንና አርሶ አደሩ በተለምዶ ይጠቀመው የነበረውን ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ለመቀየር ወደ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በትራክተር ለማረስ ታቅዶ 2 ነጥብ 44 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በትራክተር ማረስ መቻሉን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በዚህም በምርት ዘመኑ 13 ነጥብ 4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በማልማት 400 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ነው ሚኒስትሩ የገለጸው።

እስከ አሁን ባለው እንቅስቃሴ 12 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ ለዘር የተዘጋጀ ሲሆን፣ ቀሪው ደግሞ በቀጣይ የሚዘሩ ሰብሎች ዝግጁ በማድረግ የዘር ሥራዎች ይከናወናል ነው የተባለው።

ከዚህ ውስጥ 11 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል ተብሏል።

በኩታ ገጠም ያስተራረስ ዘዴ 6 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም ያስተራረስ ዘዴ ለማልማት ታቅዶ 6 ነጥብ 35 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ ዝግጁ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 5 ነጥብ 37 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር የተሸፈነ መሆኑ ተመላክቷል።

በስንዴ ምርት ልማትም በመኸር እርሻ 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴ ለማልማት እቅድ ተይዞ፣ 1 ነጥብ 19 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ በኩታ-ገጠም የአስተራረስ ዘዴ የታረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ 800 ሺሕ ሄክታር መሬት እስካሁን በዘር እንደተሸፈነ ነው የተጠቀሰው።

በበልግ ምርት 2 ነጥብ 38 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ታርሶ፣ 1 ነጥብ 9 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በዘር የተሸፈነ ሲሆን፣ ከዚህም ወደ 46 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱ ተገልጿል።


ቅጽ 4 ቁጥር 197 ነሐሴ 7 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here