የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ370 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ህንፃ ሊገነባ ነው

0
1040

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚያስገነባው አዲስ ህንፃ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ መንግሥት 370 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል መግባቱን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘገበ።

በአሁን ሰዓት እያገለገለ የሚገኘዉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ህንፃ በፈረንጆቹ በ1930ዎቹ የተሠራ ነዉ።

አዲስ የሚገነባዉ ህንፃ ለምክር ቤቱ አባላት ሥራቸውን በአግባቡ ለማከናወን ምቹ ዐውድ የሚኖረውና ሥራቸውን በተሻለ መልኩ እንዲያከናውኑ ይረዳቸዋል ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ተስፋዬ ዳባ ገልጸዋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የልዑካን ቡድን ከአረብ ኢምሬትስ አቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት ኹለቱ አገራት በሕዝብ እንደራሴዎቻቸው መሃል የሚደረግ ትብብርን ለማሳደግና የኹለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውንም ገልጸዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here