ስርዓት አልበኛ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ሊዘረጋ ነው

0
444

ስርዓት አልበኛ ነጋዴዎችን ለመቆጣጠር ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት ሊዘረጋ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር ገለፁ።

በአንዳንድ ነጋዴዎች በተለይም በዱቄት ፋብሪካዎች እና በዳቦ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን የስነ-ምግባር ችግር ለመቅረፍ ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል ያሉት ሚኒስትሯ መንግስት ደሃውን የኅብረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የሚያስገባውን ስንዴ ጥራቱን ካልጠበቀ ስንዴ ቀላቅሎ መፍጨት፤ ማዳበሪያ /ከረጢት/ በመቀየር ትስስር ላልተደረገላቸው ዳቦ ቤቶች ጭምር መሸጥ ፤ በራሳቸው የተለየ ዱቄት ማዳበሪያ ከረጢት በማሸግ ለገበያ በማቅረብ እስከ 2000 ብር ድረስ በሕገ-ወጥ መንገድ መሸጥ፤ ከተቀመጠው ዋጋ በላይ እና ከግራም በታች ጋግረው መሸጥ በአንዳንድ ዳቦ ቤቶች ላይ የተስተዋሉ ህገ-ወጥ መሆናቸውን በመጥቀስ በቀጣይ በእነዚህና መሰል ህገ-ወጥነቶች ከእኩይ ድርጊታቸው የማይታቀቡ ከሆነ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጠበቅ ያለ እርምጃ እንደሚወስድ ተጠቁሟል።

የንግዱን ስርዓት ጤናማና በውድድር ላይ የተመሰረተ ለማድረግ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ቢገኝም የግብይት ስርዓቱ ለኪራይ ሰብሳቢነት በመጋለጡ ምክንያት ስራዉን ወደ ዘመናዊ የቁጥጥር ስርዓት ለመቀየር እየሰራ መሆኑን ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here