የመጀመሪያው ስደተኞችን የጫነ አውሮፕላን ከኢትዮጵያ ወደ ጀርመን ተጓዘ

0
635

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይኦኤም 154 በኢትዮጵያ ውስጥ ተጠልለው ይኖሩ የነበሩ የሱማሊያ ስደተኞችን ወደ ጀርመን በማጓጓዝ የመጀመሪያውን ልዩ በረራ በተሳካ ሁኔታ አከናውኗል። በቋሚነት በአውሮፓዊቷ አገር ለመኖር ዕድል ተመቻቸላቸው ሱማሊያዊያን ስደተኞች በምስራቅ ኢትዮጵያ ደሎ አዶ እና ጅግጅጋ ስደተኞች ጣቢያ ተጠልለው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

ከ154 ስደተኞች ውስጥ 91 የሚሆኑት ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ወንዶች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 47 የሚሆኑት ሕፃናት መሆናቸው ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪ ስደተኞች ድርጅት በቀጣይ ወር ኅዳር አጋማሽ ላይ ኹለተኛ ዙር 220 ስደተኞችን የማጓጓ ስራ እንደሚሰራም አይኦኤም አስታውቋል። ከ220 ዎቹ ውስጥም ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አስፈላጊው ቃለ መጠይቅ እንደተደረገላቸው እና አስፈላጊውን የጤና ምርመራም ማሟላታቸው ታውቋል።  የስደተኞች ድርጅት ከኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ኤጀንሲ እና ከጀርመን መንግስት ጋር በቅንጅት በመስራት 5መቶ ስደተኞችን ከኢትዮጵያ ወደ ጀርመን በመውሰድ የተረጋጋ ህይወት እንዲኖራቸው እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here