በሦስት ወራት ውስጥ 113 የሳይበር ጥቃቶች እና ሙከራዎች ተመዘገቡ

0
919

በተያዘው በጀት ዓመት 2012 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 113 የሳይበር ጥቃቶችና  ሙከራዎች መመዝገባቸውን የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ አስታወቀ። የበጀት ዓመቱ ከጀመረበት ሐምሌ 1/2011 እስከ መስከረም 30/2012 ድረስ 42 አጥፊ ሶፍትዌሮች፣ 29 በድረ ገፅ፣ 22 በመሰረተ ልማት ቅኝቶች፣ 13 ወደ አልተፈቀደ ሲስተም ዘልቆ መግባት እና 7 የሳይበር መሠረተ ልማቶችን ሥራ ማቋረጥ አይነት ጥቃቶች መከሰታቸውን ኤጀንሲው ይፋ አድርጓል።

ባለፉት ሦስት ወራት ጥቃቶች በአገሪቱ እንዳይሰነዘሩ የቅድመ መከላከል ሥራዎችን ኤጀንሲው ሲሰራ መቆየቱን እና ጥቃት የተሰነዘረባቸውንም ከዚህ ቀደም ወደ ነበሩበት ይዞታቸው የመመለስ ሥራም መሰራቱን በኤጀንሲው የብሔራዊ አደጋ ዝግጁነትና ምላሽ መስጫ ዲቪዥን ኃላፊ አብረሃም ገብረጻዲቅ ገልፀዋል።

ኤጀንሲው በኢትዮጵያ ለተሰነዘሩ ጥቃቶች ምላሽ ሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ጥቃት ለማድረስ በቅኝት ላይ በነበሩት ላይም የመቅጨት ስራ እንደተሰራም ታውቋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ በአገሪቱ የሚሰነዘሩ የሳይበር ጥቃቶች ቅድመ የመከላከል እና ከተከሰቱ በኋላም አፋጣኝ ምላሾችን የሚሰጥ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ኤጀንሲው የአገሪቱን የኢንፎርሜሽን እና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን መሰረተ-ልማቶችን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል አቅም በመገንባት ብሔራዊ ጥቅሞችን የማስጠበቅ ተልዕኮውን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here