የኩላሊት ታማሚዋ ኢትዮጵያዊት በደቡብ አፍሪካ ህክምና እንዳታገኝ ተከለከለች

0
545

ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ ዓለም ኤርሴሎ በደቡብ አፍሪካ በደረሰባት የኩላሊት ህመም በጆሀንስበርግ ሆስፒታል ኩላሊት እጥበት ህክምና ስታገኝ የነበረ ሲሆን የደቡብ አፍሪካዊ ዜግነት ሰለሌላት ሆስፒታሉ ህክምናውን እንዳታገኝ አድርጓታል።

ጉዳዩን ለጆሃንስበርግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ብታቀርብም ፍርድ ቤቱ ከሔለን ጆንሰን ሆስፒታል ጎን በመቆም ደቡብ አፍሪካ ዜግነት ስለሌላት እና የተረጋገጠ ቋሚ የዜግነት ማስረጃ ማቅረብ አልቻለችም በማለት ህክምናውን እንዳታገኝ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ አስተላልፏል።

ታማሚዋ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ህመሙ በደረሰባት ወቀት በደቡብ አፍሪካ ሕገ መንግሥት ላይ የሚገኘውን ሁሉም ሰው የራሱ ህልውና፣ የእኩልነት እና ህክምና የማግኘት መብት እንዳለው የሚጠቅስ አንቀጽ አንስታ ብትከራከርም ተቀባይነት ሳታገኝ ቀርታለች።

አሁን የታማሚዋ ኩላሊት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት ያቆመ ሲሆን ይህም የሆነው በወቅቱ ተገቢውን ወሳኔ ባለማግኘቷ እንደሆነ ትገልፃለች። ከዘጠኝ ዓመታት በኋላ ጉዳዩን ያዩት ዳኛ በወቅቱ ምን ተከስቶ እንደንደነበር ግልፅ አይደለም ብለዋል።

አያይዘውም አመልካቿ የድንገተኛ ጊዜ ህክምናን እንዳልተከለከለች እና የጤናዋ ሁኔታ በተረጋጋበት ወቅት ወደ ሀገሯ ተመልሳ ቋሚ ህክምና ማግኘት እንደምትችል ገልፀዋል።

ሔለን ጆንሰን ሆስፒታል ያቀረበው ማስረጃ፣ በወቅቱ ድንገተኛ ለኩላሊት እጥበት የሚያገለገሉ መሣሪያዎች እጥረት በማጋጠሙ አዲስ ታማሚዎችን መቀበል አለመቻሉን በፍርድ መዝገቡ ላይ ተገልጿል።

ቅጽ 1 ቁጥር 50 ጥቅምት 8 2012

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here