1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ‹‹የከሰረው ድርጅት›› በደረሰኝ አጭበርብሯል ተባለ

0
850

በሰበታ የሚገኘው ቢኤምቲ የኬብል ፋብሪካ ሀሰተኛ ደረሰኝ በማቅረብ 1 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ሊያሳውቅ ሲል መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ። ድርጅቱ ወደ 670 ሚሊዮን ብር የግብር ዕዳ አለበት ያለው ሚኒስቴሩ፣ ቢኤምቲ ሀሰተኛ ደረሰኝ ከሚያመርቱ ድርጅቶች ደረሰኝ ከመግዛቱ በተጨማሪ ሌሎች ግብር ከፋዮች የከፈሉትን ብር በተመላሽ ሊወስድ ሲሞክር በመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች መያዙ ተነግሯል። በቱርክ ባለሃብቶች የተመሰረተው ቢኤምቲ በኢትዮጵያ ቀዳሚ የኬቤል አምራቾች መካከል ይመደባል። የተለያዩ የኤሌክትሪክ ኬብሎችን፣ ፋይበር ኦፕቲክስን ጨምሮ የሚያመርተው ድርጅቱ ወደ ሦስት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ካፒታል እንዳለው ድረ ገጹ ያሳያል።

ቅጽ 1 ቁጥር 50 ጥቅምት 8 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here