ከኢንዱስትሪ ፓርኮች 140.6 ሚሊየን ዶላር ገቢ ተገኘ

0
778

በኢንዱስትሪ ፓርኮች ወስጥ የሚገኙ ፋብሪካዎች 140 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ ምርቶች ወደ ውጭ መላካቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታውቋል። ይህ ባለፈው በጀት ዓመት ከተመዘገበው ጋር ሲነፃፀር የ57 በመቶ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን ከተላኩት ምርቶች መካከል ጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳ ውጤቶች፣ የመዳብ ኤሌክትሪክ ገመዶች ዋነኞቹ ናቸው።

ከፍተኛ ድርሻ የሚይዘው ምርት ከሃዋሳ፣ ቦሌ ለሚ እንዲሁም ኢስተርን አንዱስትሪ ፓርኮች የተላኩ ሲሆን የታቀደውን 71 ነጥብ 4 በመቶ ማሳካት መቻሉን ኮሚሽኑ አስታውቋል። ኢትዮጵያ በ2012 በድምሩ 30 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ይኖሯታል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ ላይ ተሳትፏቸውን እንዲያጎለብቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከዚህ ቀደም ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ቅጽ 1 ቁጥር 50 ጥቅምት 8 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here