የገዳ እና ሰላም ትምህርት በማስተርስ ደረጃ ሊሰጥ ነው

0
537

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት ባደረገው ስብሰባ የገዳ እና ሰላም ትምህርትን በማስተርስ ደረጃ ሊሰጥ መሆኑን አስታውቋል።
ይህም የገዳ ስርዓትን በማስተርስ ደረጃ በመስጠት ዩኒቨርስቲውን ቀዳሚ ሲያደርገው በተለይም ስርዓቱን ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ እና ለጥናት እና ምርምር ትልቅ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይታመናል። የገዳ ስርዓት ዘመን ተሻግሮ ለትውልድ ባስተላለፈው ጥሩ ባህላዊ እሴት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በዓለም የማይዳሰስ ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን በኢትዮጵያ የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ዘንድ ባሕላዊ አስተዳደራዊ ስርዓት ሆኖ ለዘመናት አገልግሏል።

ቅጽ 1 ቁጥር 50 ጥቅምት 8 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here