መድኃኒት ከተላመደ የቲቢ በሽታ ከተስፋፈባቸው 33 ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ መውጣቷ ተገለጸ

0
1147

መድኃኒት ከተላመደ የቲቢ በሽታ ከተስፋፈባቸው 33 አገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ መውጣቷን ጤና ሚኒስቴር አሰታወቀ።
ኢትዮጵያ ዓለም ዐቀፍ መድኃኒት የተላመደ የቲቢ በሽታን መግታት የድርጊት መርሃ ግብር ተቀብላም እየሠራች ነው። በምሥራቅ፣ መካከለኛና ደቡብ አፍሪካ ዓመታዊ የቲቢ በሽታ ምርመራ ላብራቶር የማጠናከሪያ ውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በአገሪቱ በቲቢ መከላከል ዙሪያ የተሠሩ ሥራዎች አበረታች ለውጥ እያሳዩ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሯ በዋቢነትም በዓለም መድኃኒት የተላመደ የቲቢ በሽታ ከተስፋፈባቸው 33 አገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ መውጣቷን በመድረኩ ተመላክቷል።
ቲቢን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሥራ የመመርመሪያ ቁሳቁስ የሞለኪዩላር ምርመራ ቁጥር ከአገሪቷ ፍላጎት አንፃር አለመመጣጠን፣ የምርመራ ጊዜ መዘግየት፣ የምርመራ አቅም ማነስና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች እንደተግዳሮት ተጠቅሰዋል።
ከ19 ሀገራት የተውጣጡ የላብራቶሪ ባለሙያዎች፣ አጥኚዎች፣ የአገራት ተወካዮች፣ ከዓለም ጤና ድርጅትና የተለያዩ አጋር አካላት መገኘታቸው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 201 ጷጉሜን 5 2014

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here