የላሊበላ ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ጥገና ተጠናቀቀ

0
662

ከ700 ሺሕ ዶላር በላይ ወጪ የተደረገበት የላሊበላ ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ጥገና ተጠናቆ ባሳለፍነው ረቡዕ፣ ኅዳር 12 ተመርቋል።
ከላሊበላ በ11ዱ ፍልፍል አብያተ ክርስትያናት መካከል የሆነው ቤተ ጎልጎታ ሚካኤል ጥገና ወጪ የተሸፈነው በአሜሪካ እና ‹ወርልድ ሞኑመንት› ነው ተብሏል።
ጥገናው ጥቅምት 2009 እንደተጀመረ የተገለጸ ሲሆን፣ ከቤተ ገብርኤል-ሩፋኤል ጥገና የተገኙ ልምዶች አጋዥ መሆናቸው ተመልክቷል።
የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ የተጋረጠው የመፍረስ አደጋ አሁንም ስጋት እንደሆነ ነው። ጥገናውን ለማከናወንም የመንግሥትና ሌሎች ባለድርሻዎች ተሳትፎ የተጠየቀ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የአማራ ክልል መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸው ይታወሳል።
በምርቃው መርሐ ግብር የተገኙት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ከአሜሬካ ኤምባሲ ጋር በመተባበር በመካሔዱ የቅርስ ጥገናዎች ብርቱ ጥንቃቄ እንደሚደረግ አውስተዋል። ቅርሶቹ የመጭዎቹ ትውልዶችም ሀብት በመሆናቸው ጥንቃቄ በተሞላበበት መንገድ እንደሚመለከቷቸውም አንስተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here