የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ አንደኛ ዓመቱን አከበረ

0
346

በኢትዮጵያ ለሚሰሩ የልማት ስራዎች ድጋፍ ለማድረግ በውጭ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ገቢ ለመሰብሰብ በኢትዮጵያዊያን እና በትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተቋቋመው የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ አንደኛ ዓመት ክብረ በዓሉን አከበረ።

ትረስት ፈንዱ ከተመሰረተበት ካለፈው የፈረንጆች ዓመት ጥቅምት 22/2018 ጀምሮ በርካታ ድጋፎችን ማሰባሰብ የቻለ ሲሆን በአንድ ዓመት ጉዞው 5 ሚሊዮን 74ሽሕ ዶላር መሰብሰብ እንደቻለ ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ በዋናነት ሲረዱ የቆዩትን ከ26 ሽሕ 500 በላይ ለጋሾችንም በይፋ አመስግኗል።

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ትረስት ፈንድ ከ300 በላይ ፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን መቀበሉንና አብሮ ለመስራት በሒደት ላይ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል። በበጎ ፈቃደኞች የሚመራው ትረስት ፈንዱ በቀጣይ ስራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here