መነሻ ገጽዜናወፍ በረር ዜናከመሬት ጋር በተገናኘ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መቆጣጠር የሚያስችል ፕሮጀክት ወደ ሥራ መግባቱ ተነገረ

ከመሬት ጋር በተገናኘ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን መቆጣጠር የሚያስችል ፕሮጀክት ወደ ሥራ መግባቱ ተነገረ

በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት እና መሬት ነክ አገልግሎቶች ጋር በተገናኘ የሚታዩ ወንጀሎችን መቆጣጠር የሚያስችል የ200 ሚሊዮን ብር ፕሮጀከት ወደ ሥራ ማስገባቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተናገረ።

በከተማ ዐቀፍ ደረጃ የሚታየው የሙስና ችግር ተገልጋዩ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ ከማሳደሩ ባለፈ የሀብት ብክነት እንዲፈጠር ማድረጉን  የተናገሩት የቢሮው ኃላፊ ቀነአ ያደታ (ዶክተር)፣ የአሰራር ክፍተቶች ለሙስና ተጋላጭ እያደረጉ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።

ከመሬት ጋር በተገናኘ ያሉትን ችግሮች ለመቅረፍ እና የሕግ ተጠያቂነትን ለማስፈን ከተማ አስተዳደሩ እንቅስቃሴ እያደረገ ቢገኝም በሚፈለገው ልክ ግን ለውጥ እየመጣ እንዳልሆነ የተነገረ ሲሆን፣ ወንጀሉን በዘላቂነት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን መጠቀም አሰፈላጊ ሆኖ መገኘቱ ተነግሯል።

ለእዚህም ሲባል ከተማዋን ያማከለ የአንድ ማእከል የቴክኖሎጂ ስርዓት ለመዘርጋት እንቅስቃሴ መጀመሩን የጠቀሱት ኃላፊው፤ ለቴክኖሎጂው 200 ሚሊዮን ብር እንደሚወጣበት አሳውቀዋል። ቴክኖሎጂው ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ ሲገባ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እና ወረዳዎች ያለውን የመሬት አያያዝ መረጃ ከመከታተል አንጻር ትልቅ ሚና እንደሚወጣ የጠቆሙት ኃላፊው፣ ወጪው በመንግሥት ይሸፈናል ብለዋል።


ቅጽ 4 ቁጥር 203 መስከረም 14 2015

- ይከተሉን -Social Media
ተዛማጅ ጽሑፎች

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here

- Advertisment -
Ads

የቅርብ ጊዜ ጽሑፎች