በሰሜኑ ጦርነት በአፋርና አማራ ክልል 2831 ንጹሐን መገደላቸው ተገለጸ

0
741

በሰሜኑ የኢትዮጵያ ጦርነት የተፈጸሙ ሰብዓዊ መብት ጥሰቶችና ወንጀሎችን በተመለከተ የተከናወኑ የወንጀል ምርመራ ሥራዎች እንዲያከናውን የተቋቋመው ቡድን፣ በአማራና አፋር ክልሎች በተከናወነው ምርመራዎች 2 ሺሕ 831 ሰዎች መገለዳቸው በምርመራ ማረጋገጡን ይፋ አድርጓል።

የፍትሕ ሚኒስቴር በምርመራ ውጤቱ ላይ በሰጠው መግለጫ፣ 452 ሰዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙ የታወቀ ሲሆን፣ 36 ሰዎች የደረሱበት ቦታ ሳይታወቅ ተሰውረዋል ብሏል።

የምርመራ ቡድኑ በኹለቱ ክልሎች 865 ሺሕ 627 ኩንታል እህል መውደሙን፣ 411 ሺሕ  የቁም እንስሳት መገደላቸው፣  ከ2500 በላይ የጤና ጣቢያና ሆስፒታሎች መውደማቸውን እና 26 ሺሕ 334 ቤቶች ደግሞ መቃጠላቸው መታወቁን የምርመራ ቡድኑ ማረጋጡን ይፋ አድርጓል።

በምርመራው 175 ወረዳዎችን ለማካለል ተሞክሮ በተሠራው የሰብዓዊ መብት ጥሰት የምርመራ ሥራ በአማራ ክልል 9 ሺሕ 552 የምስክሮች ቃል በአፋር ክልል 517 የምስክሮች ቃል የተሰማ ሲሆን፣ በኹለቱም ክልሎች 3 ሺሕ 387 የሰነድ ማስረጃ፣ 2 ሺሕ 599 የፎቶና የተንቀሳቃሽ ምስል ሰነዶችም ቀርበው ምርመራ እንደተደረገባቸውም ተገልጿል።

በተጨማሪም ከፍርድ ውጪ ግድያ ከተፈጸመባቸው 2 ሺሕ 831 ንጹሐን ዜጎች አብዛኛው በሽብርተኝነት በተፈረጀው ሕወሓት የተፈጸመ የተባለ ሲሆን፣ በሰሜን ሸዋ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ውስጥ ደግሞ የሽብር ቡድኑ ሸኔ ከሕወዐት ጋር በቅንጅት ግድያውን መፈፀሙ እንደተረጋገጠ ተጠቅሷል።


ቅጽ 4 ቁጥር 203 መስከረም 14 2015

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here