ሴታዊት ከስዊድን ኤምባሲ እና ዩኤን ውመን ጋር በመተባበር ምን ‹‹ለብሳ ነበር የሚል›› ዐውደ ርዕይ አዘጋጅታለች።
ዐውደ ርዕዩ ሴቶች በሚደፈሩ ጊዜ አለባበስን ለጥቃቱ ምክንያት በማድረግ መልሶ ተጠቂዎችን የመውቀስ ልምድን ለመቀየር ያግዛለ በሚል የተዘጋጀ ነው፡፡
ይህን መነሻ በማድረግም ዐውደ ርዕዩ ሴቶች በተደፈሩ ጊዜ የለበሱትን ልብስ ያሳያል ተብሏል፡፡ ከኅዳር 18 እስከ ታኅሣሥ 1/2011 የሚቆየው መርሐ ግብሩ በአዲስ አበባ ሙዚየም ይደረጋል፡፡ የመግቢያ ክፍያ እንደሌለው ያሳወቁት አዘጋጆቹ ፍላጎቱ ያላቸውን በሙሉ ጋብዘዋል፡፡