በደራሲና ሐያሲ ዓለማየሁ ገላጋይ የተጻፈው “ታለ በዕውነት ሥም” የተሰኘው አዲስ ልብ ወለድ መጽሐፍ ዛሬ በገበያ ላይ ውሏል። አዲስ ማለዳ ከደራሲው ባገኘችው መረጃ መጽሐፉ የሚያጠነጥነው በእውነት ላይ ሲሆን በዚህ ዙሪያ ለመጻፍ የተነሳሳበትን ምክንያትም ሲያስረዳ “ያለንበት ዘመን እውነት የተሳከረበት በመሆኑ ያንን መነሻ በማድረግ ነው የጻፍኩት” ብሏል። መጽሐፉ በ220 ገጽ የተቀነበበ ሲሆን በ100 ብር ዋጋ እንደሚሸጥ ታውቋል።
ዓለማየሁ ገላጋይ እስካሁን አዲሱን መጽሐፉን ጨምሮ 12 መጽሐፍትን ላንባቢያን ያቀረበ ሲሆን አጫጭር ምልከታዎቹን በተለያዩ የሕትመት ውጤቶች ላይ በማስነበብ እንዲሁም በተለያዩ መጽሐፈት ዙሪያ ሒስ በመስጠት ይታወቃል።